Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና እስራኤል በእግር ኳስ ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና የእስራኤል እግር ኳስ ማኅበራት ሊቀመንበሮች በዘርፉ የሁለትዮሽ ትብብርን ለማሳደግ የመግባቢያ ስምምነት እንደሚፈራረሙ በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከእስራኤል አቻዉ ጋር ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማካሄድ ወደ እስራኤል መግባቱ ተገልጿል።

የወዳጅነት ጨዋታዎቹ በሁለቱ የእግር ኳስ ማህበራት መካከል እያደገ ያለው ግንኙነት ቅጥያ መሆናቸውን ነው ኤምባሲው ያስታወቀው፡፡
ሁለተኛው ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት ሐሙስ እለት የእስራኤል እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማኅበራት በዘርፉ የሁለትዮሽ ትብብርን ለማሳደግ የመግባቢያ ስምምነት እንደሚፈራረሙ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከእስራኤል አቻዉ ጋር የሚያደርገው የመጀመርያው ጨዋታ ዛሬ በ12 ሰዓት፤እንዲሁም 2ኛው ጨዋታ ሐሙስ በ5 ሰዓት ይደረጋል ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.