Fana: At a Speed of Life!

ምርጫው ያለ ምንም ችግር መጠናቀቁንና ከፍተኛ ፋክክር የታየበት ነው – አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላለፋ፡፡

ምርጫው ያለ ምንም ችግር መጠናቀቁንና ከፍተኛ ፋክክር የታየበት ነበር ብለዋል፡፡

ምርጫው እንዳይካሄድ የሚፈልኩ አካላት የነበሩ ቢሆንም ምርጫውን በተሳካ ሁኔታ ማካሄድ እንደተቻለ ገልፀዋል

በምርጫው ሒደት የድምፅ መስጫ ወረቀት እጥረት የገጠመ ቢሆንም ችግሩ ተቀርፎና ህዝቡ በትግስት በምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምፅ መስጠት መቻላቸውን ገልፀው ለመላው ህዝብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ርዕሰ መስተዳድሩ ምርጫው በሰላም መጠናቀቁን አስታውቀዋል

ህዝቡም ከትላንት ለሊት አስራ አንድ ሰዓት ጀምሮ በምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምፅ ለመስጠት ያደረገው ጥረት የሚደነቅ ነበር ብለዋል በዛሬው እለትም የነበረው የድምፅ መስጠት ሒደት ስኬታማ እንደነበር አስታውቋል

በክልሉ ሲወዳደሩ የነበሩ የፖለቲካ ፖርቲዎችም ምርጫው በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን በመግለፅ አመስግነው ፣ከምርጫው በኋላም በዚሁ መንገድ መቀጠል ይገባዋል።

በቀጣይም ድህነትን ለማሸነፍ በሚደረግ ጥረት ላይና በልማት ስራዎች ላይ ማተኮር ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል

መራጩን ህዝብ ጨምሮ የፀጥታ ሀይሉ የመገናኛ ብዙሃን የምርጫ አስፈፃሚዎችና በምርጫው ሒደት ሚና የነበራቸው አካላት በሙሉ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

በብርሃኑ በጋሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.