Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ድምጽ የተሰጠባቸው 98 በመቶ የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ክልል ገብቷል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ክልል ደረጃ 98 በመቶ ድምጽ የተሰጠባቸው የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ክልል መግባት እንደቻለ የሲዳማ ክልልና የደቡብ ክልሎች ምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በደቡብ ክልል የተቀሩት የምርጫ ቁሳቁሶችም ወደ ምርጫ ክልል ከተወሰኑ ሰዓታት በኋላ የሚገባ መሆኑን የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ፍሬው በቀለ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪ በሲዳማ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ እስከ ስድስት ሰዓት ድረስ ተጠቃሎ ወደ ምርጫ ክልል እንደሚገባ ሀላፊው ተናግረዋል፡፡

በሀዋሳ ከተማ በትናንትናው ዕለት ቆጠራው ተጠናቆ የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ክልል ተሰባስበው መጠናቀቃቸውን ሃላፊ ገልፀዋል፡፡

በሲዳማ ደረጃ ትናንት የተካሄደው የድምፅ መስጠት ሂደት ስኬታማ ነበር ያሉት ሃላፊው፥ የደቡብ ክልል የድምፅ መስጠት ሒደትም በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

ከተለያዩ የፖለቲካ ፖርቲዎች የቀረቡ ቅሬታዎችም በሚገባ የማጣራትና ውሳኔ የመስጠት ስራ ይከናወናል ብለዋል ሃላፊው፡፡

በማጓጓዝ ስራውም ምንም ችግር አለመግጠሙን የገለጹ ሲሆን፥ መራጩን ህዝብ ጨምሮ የፀጥታ ሀይሉ፣ የመገናኛ ብዙሃን፣ የምርጫ አስፈፃሚዎችና በምርጫው ሒደት ሚና የነበራቸውን አካላትን አመስግነዋል።

በብርሃኑ በጋሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.