Fana: At a Speed of Life!

ከመተከል ዞን ተፈናቅለው በቻግኒ ራንች መጠለያ ጣቢያ የነበሩ ዜጎች ወደቀያቸው መመለስ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ከመተከል ዞን ተፈናቅለው በቻግኒ ራንች መጠለያ ጣቢያ የነበሩ የወምበራ ፣ የድባጤ ፣ የቡለንና የጉባ ተፈናቃዮች ወደ ተዘጋጀላቸው ስፍራ እየተለመሱ ነው።

የኮማንድ ፖስቱ የቴክኒክ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ቀለሙ ሙሉነህ እንደተናገሩት፥ በቻግኒ ራንች ከሚገኙ ከ50 ሺህ በላይ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደየወረዳቸው የተመረጡ ስፍራዎች የመመለሱ ስራ በጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሰብዓዊ ድጋፎቹ በዘላቂነት እስኪቋቋሙ ድረስ የድርጊት መርሃ ግብሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የድባጤ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሙሉዓለም ዋዊያ በበኩላቸው፥ የወረዳችንን ተፈናቃዮች ለመቀበል አሰፈላጊውን ዝግጅት አድርገናል ብለዋል።

የቡለን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ግዛቱ ነሲ፥ ህብረተሰቡ ወደ ቀዬው ሲመለስ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የመሠረተ ልማትና የሰብዓዊ ድጋፎችን ከወዲሁ በማዘጋጀት ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

የሁለቱ ወረዳ ሃላፊዎች አያይዘውም፥ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የተለያዩ የስራ ዕድል አማራጮች መዘጋጀታቸውንና ለዚህም ህብረተሰቡ ያሳየው ተነሳሽነትና ድጋፍ አድንቀዋል።

በመጀመሪያው ዙር የዳንጉርና የማንዱራ ወረዳ ተፈናቃዮች ወደየወረዳቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.