Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ሕብረት በድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ያጋጥሙ የነበሩ ክፍተቶችን ለመሙላት የተደረገውን ጥረት አደነቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ሕብረት ባለፈው ሰኞ በተካሄደው 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ በድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ያጋጥሙ የነበሩ ክፍተቶችን ለመሙላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያደረገውን ጥረት አደነቀ።
ህብረቱ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን ለመታዘብ በርካታ ታዛቢዎችን ምርጫው በተካሄደባቸው የተለያዩ አካባቢዎች አሰማርቶ እንደነበር ገልጿል።
ዛሬ በሰጠው መግለጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቅ መቻሉን መታዘቡን አውስቷል።
ህብረቱ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በርካታ ጠንካራ ጎኖች እንደነበሩት ገልጾ በተለይም የምርጫ ቦርድ በሂደቱ ሲያጋጥሙ የነበሩ ክፍተቶችን ለመሙላትና ወቅታዊ ምላሽ ለመስጠት ያደረገውን ጥረት አድንቋል።
መራጮችም በነቂስ ወጥተው በምርጫ እንደተሳተፉ አመልክቶ ድምጽ ለመስጠት በትዕግስት መጠበቃቸው መልካም እንደነበር መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል።
ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሂደቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበራቸው መመልከቱን ህብረቱ ገልጿል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.