Fana: At a Speed of Life!

የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ከዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ዳይሬክተር ከሚመራው የልዑካን ቡድን ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ከዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ዳይሬክተር ከሚመራው የልዑካን ቡድን ጋር ተወያየ፡፡
በውይይቱ የሁለቱን ድርጅቶች አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ንጉሡ ጥላሁን ዓለም ባንክ ከዚህ በፊት ከኮሚሽኑ ጋር ያለውን ጠንካራ ወዳጅነት አድንቀው ወደፊት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አቅርቦት እና የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተቋማትን የማጠናከር ሥራ እንዲሁም በቅርቡ ለሚጀመረው የሥራ ዝግጁነት ፕሮግራም ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
የልዑኩ መሪ ኦስማን ዲዮኔ በበኩላቸው ዓለም ባንክ በመሠረተ ልማት፣ በግብርና፣ በከተማ ልማትና በ አጠቃላይ በድህነት ቅነሳ ላይ በመሳተፍ እድገት ተኮር እንቅስቃሴዎችን እንደሚያበረታታ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ያሏትን የተፈጥሮ ኃብቶችና እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓይነት መሠረተ ልማቶቿን በመጠቀም በግብርና እና ቱሪዝም ሴክተሮች በርካታ የሥራ ዕድሎችን የመፍጠር ዓቅም እንዳላት አሳስበዋል።
የእውቀት ሽግግርና አመርቂ የሥራ ዕድሎች በመፍጠር የኢትዮጵያን የሥራ ዕድል ፈጠራ በሞዴልነት ለማሳየት የዓለም ባንክ ተቋማዊ ድጋፉን እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ከሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.