Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ ድርድር የጋራ ተጠቃሚነትን ባከበረ መንገድ እንዲካሄድ የአሜሪካ “ብላክ ኮከስ” አባላት ጠየቁ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት በማድረግ ድርድር እንዲካሄድ የአሜሪካ ኮንግረስ “ብላክ ኮከስ” አባላት ጠየቁ።

በግድቡ ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ አሁንም የጋራ ተጠቃሚነትን እና ትብብር መሰረት ያረገ ሰላማዊ ድርድር ሊያደርጉ ይገባል ብሏል።

ይህ ድርድር የጋራ ተጠቃሚነትን እና ዓለም አቀፍ ህጎችን ያከበረ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት አባላቱ።

ግድቡ በአህጉሩ ትልቁ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ በመሆኑ ኤሌክትሪክ ለጎረቤት ሀጋራት በመላክ መልካም አጋጣሚ ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል።

የ“ብላክ ኮከስ” አባላቱ አሜሪካ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተዋንያን በፈረንጆቹ 2015 ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ የፈረሙትን የሶስትዮሽ ድርድር ሊያከብሩ ይገባል ብለዋል።

አሜሪካ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ የአፍሪካ ህብረትን በማማከር ጠቃሚ ሚናውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም ወገኖች ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሰላማዊ ድርድር እንዲካሄድ የአፍሪካ ህብረት ወሳኝ ሚና አለውም ነው ያሉት።

የአሜሪካ ኮንግረስ “ብላክ ኮከስ” አባላት የህዳሴው ግድብ ለአህጉሪቱ ካለው ፋይዳ አንጻር እንዲጠናቀቅ ሰላማዊ ድርድርን እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.