Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራን በኬንያ ለመተግበር ማቀዷ የሚደነቅና በደስታ የምንቀበለው ነው -የኬንያ የደን ልማት ሃላፊ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኬንያ መንግስት ጋር በመቀናጀት አንድ ሚሊየን የሚሆን የችግኝ ተከላ ሊያከናውን ነው፡፡

ኤምባሲው በኬንያ የችግኝ ተከላ ለማካሄድ በሚችልበት ሁኔታ ላይ አምባሳደር ሲራጅ ረሺድ ከኬንያ የደን ልማት ኃላፊ ጁልየት ካማው ጋር ውይይት አካሄዷል፡፡

አምባሳደር ሲራጅ የአረንጓዴ  አሻራ ሌጋሲ በኬንያ ሀገር ለመተግበር ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል የቀረበው ጥያቄ በኬንያ መንግስት ተቀባይነት በማግኘቱ አመስግነዋል፡፡

አያይዘውም የችግኝ ተከላው በአካባቢዎች መራቆት ምክንያት እየደረሰ ያለውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመቀነስ ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል።

ለዚህም በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ችግኝ በመዘጋጀቱና ዝግጅት በመጠናቀቁ  የችግኝ ተከላ የሚካሄድበትን አካባቢ ተለይቶ የሚሰጥበት፣ ችግኙን ለመትከል ተስማሚ ጊዜ፣ የተዘጋጁ ችግኞችም የተለያዩ አይነቶች በመሆናቸው ለኬንያ ተስማሚ የሚሆኑት የችግኝ አይነቶች የመለየት ስራ መሰራት አስፈላጊ መሆኑን ገለፃ አድርጓል፡፡

የኬንያ የደን ልማት ኃላፊ በበኩላቸው ÷የኢትዮጵያ መንግስት የአረንጋዴ አሻራን በኬንያ ለማካሄድ  አቅዶ ዝግጅት ማጠናቀቁ የሚደነቅና ሀገራቸው የችግኝ ተካላውን በደስታ የምትቀበል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ናይሮቢ አቅራቢያ ልዩ ስሙ ጎንግ ሂል አካባቢ ከአንድ ሚልየን ችግኞች በላይ መትከል የሚቻል መሆኑን እና የተወሰኑ ችግኞችም በናይሮቢ ከተማ ንጎንግ ጎዳና እንደሚተከል ተናግረዋል።

ለዚህም አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ የችግኝ ተከላው በመጪው ጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ ማካሄድ የሚቻል መሆኑን ማብራራታቸውን በኬንያ ከኢጥዮጵያ ኤምባሲ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.