Fana: At a Speed of Life!

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን ቢያንስ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ወደ ሃገራቸው ለመመለስ እየተሰራ ነው- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን ቢያንስ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ወደ ሃገራቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸው ኢትዮጵያ 6ኛውን ሃገራዊ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ ማከናወን በመቻሏ አለም አቀፍ ትኩረት ማግኘቷን ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ምርጫውን ስታካሂድ የተለየ ነውጥ እና ብጥብጥ እንደሚፈጠር የጠበቁ አካላት ባይጠፉም ምርጫው ፍፁም ኢትዮጵያዊነት የፀናበት እና ኢትዮጵያ አሸንፋ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ምሳሌ መሆን የቻለችበት እንደነበር የሃገር ውስጥም ሆነ የውጭ ታዛቢዎች መግለጫ ማረጋገጡን ተናግረዋል፡፡
በዲፕሎማሲው ዘርፍ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ሩሲያ በማቅናት ኢትዮጵያ ከሃገራቱ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ እና ባለ ብዙ ወገን ግንኙነት ማስቀጠል በምትችልበት ሁኔታ ላይ እየመከረ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
በዚህም ሃገራቱ ኢትዮጵያ ከህዳሴ ግድብ፣ ከትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ስራ እና ከድንበር ግጭት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ መግለጻቸውን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡
በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲው መስክ ደግሞ በተለይም በሳዑዲ አረቢያ በመኖሪያ ፈቃድ ሳቢያ እየተንገላቱ የሚገኙ ዜጎች ቢያንስ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ዜጎቹን መመለስ ብቻ ሳይሆን መብታቸውም እንዲጠበቅ ከተለያዩ ተቋማት ተውጣጥቶ ወደ ሳውዑዲ አረቢያ ያመራው ሉዑክ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ልዑኩ የስደተኞቹን ትክክለኛ ቁጥር እና ዜግነታቸውን የመለየት ስራ እያከናወነ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡
በሶዶ ለማ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.