Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ከሳኡዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር መከረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ከሳኡዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ዜጎች ወደ አገር በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ መክሯል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል መስፍን ሻዎ የተመራው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ጋር በመሆን ነው ከሳዑዲ አረብያ ሃላፊዎች ጋር ውይይት ያደረጉት ፡፡

ልዑኩ ከሳኡዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ተሚሚ አል-ደውሰሪ እና ከሳኡዲ አረቢያ የአገር ግዛት ሚኒስቴር ልዩ የደህንነት አማካሪ ጄኔራል ጀምዓን አዛህራኒ ጋር በሳኡዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች መብትና ደህንነት በሚከበርበት እና ወደ አገር በሚመለሱ ዜጎች ዙሪያ ውይይት በማድረግ ወደ ዝግጅት ገብተዋል።

በዚህም የሳኡዲ አረቢያን የድንበር ደህንነት ሥርዓት ጥሰው የገቡ፣ የአገሪቱን የመኖሪያ ፍቃድ እና የሥራ ፈቃድ ህግጋትን ተላለፈው የሚገኙ ዜጎች ሰብዓዊ ክብራቸው ተጠብቆና በገዛ ፍቃዳቸው በተፋጠነ ሁኔታ እና በሁለቱ አገራት መንግስታት የጋራ ትብብር ወደ አገራቸው የመመለስ ሂደት በቅርብ ቀን የሚጀመር ይሆናል ተበሏል።

የልዑካን ቡድኑ በጂዳ ሹመይሲ እስር ቤት ጉብኝት በማድረግ ታራሚዎችን ያሉበትን ሁኔታ በመመልከት፣ በማነጋገር፣ በማበረታታት እና በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ መግለጻቸውን በሳውዲ አረቢያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.