Fana: At a Speed of Life!

ከፑሽኪን አደባባይ ወደ ጎተራ ማሳለጫ የሚወስደው መንገድ  ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ከፑሽኪን አደባባይ ተነስቶ በጎፋ ማዞሪያ ወደ ጎተራ ማሳለጫ የሚወስደው ዋና የመንገድ ክፍል ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት ተደርጓል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከፑሽኪን አደባባይ ወደ ጎተራ ማሳለጫ የሚወስደው መንገድ 320 ሜትር ርዝመት ያለው የዋሻ ስራን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በመጠናቀቁ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል፡፡

በቀጣይ የመንገድ ፕሮጀክቱ ቀሪ የግንባታ ስራዎችም በተያዘላቸው ጊዜ መሰረት እንዲጠናቀቁ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡

የመንገዱ በዚህ ደረጃ መሰራት ቄራ አካባቢ የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ  እንደሚቀርፍ ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.