Fana: At a Speed of Life!

የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ በስኬት በመጠናቀቁ ደስታውን ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 72ኛው ልዩ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ሚኒስትሮች ምክር ቤት አትዮጵያ ያካሄደቸው 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ በስኬት በመጠናቀቁ ደስታውን ገልጿል፡፡

ለምርጫው ስኬት በተለያየ መልኩ ድጋፍ ላደረጉ አባል ሃገራት እና ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ምክር ቤቱ በደቡብ ሱዳን ፣ በሶማሊያ ፣ በኮቪድ19 እና በአባል ሃገራት ተፈናቃዮች መልሶ ማቋቋም ዙሪያ በበይነ መረብ ውይይት አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ልዑካንን የመሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ 6ኛው ብሄራዊ ምርጫ ሰላማዊና በስኬት መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

የሶማሊያ ፖለቲካ ሃይሎች በምርጫ ዙሪያ የነበራቸውን ልዩነቶች በውይይት በመፍታት፣ በሃገራቸው ምርጫውን ለማካሄድ ላሳዩት ቁርጠኝነት እና ዝግጅት አምባሳደር ብርቱካን አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በደቡብ ሱዳን ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻል የሚታይበት መሆኑን ጠቁመው በ2018 በአዲስ አበባ በተፈረመው ስምምነት መሰረት በሃገሪቱ ከሁሉም የተውጣጣ ብሄራዊ ሰራዊት የመገንባቱ ሂደት በተቀመጠው አኳሃን ተግባራዊ እንዲደሬግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ እየገጠሙ ያሉ ችግሮች መፍትሄ ያገኙ ዘንድ ኢትዮጵያ የበኩሏን ድጋፍ እንደምታደርግም አረጋግጠዋል፡፡

ኮቪድ19ን ከመከላከል ጋር ተያይዞ የአባል ሃገራትን የክትባት ተደራሽነት ለማስፋት እና የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማቅረብ በኢጋድ በኩል አባል ሃገራቱ ጥረት ማድረግ አለባቸው ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.