Fana: At a Speed of Life!

በአጣዬ አካባቢ የተቋቋመው የኮማንድ ፖስት የፈፀማቸውን ስራዎች ገመገመ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአጣዬና አካባቢው ተፈጥሮ የነበረውን ችግር ለመፍታት የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ስራ ከጀመረ አንስቶ ያከናወናቸውን ተግባራትና የተገኙ ለውጦችን በከሚሴ ከተማ ገምግሟል።

ኮማንድ ፖስቱ ለማከናወን ያቀዳቸው፣ የተፈጠረውን ግጭት የማስቆምና ወደ መደበኛ ሁኔታ የመመለስ ፣ ማህበራዊና አስተዳደራዊ ሁኔታዎችን ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ ፣ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተወሰዱ እርምጃዎችና ጥፋተኞችን ወደ ፍርድ ለማቅረብ የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ እንዲቀጥል ለማስቻል እና በአፈፃፀሙ ላይ የታዩ ክፍተቶችን ለመፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ነው ግምገማውን ያደረገው።

በግምገማው የዞንና የወረዳ የኮማንድ ፖስቱ አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን ለቀጣይ የስራ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.