Fana: At a Speed of Life!

ከጣቢያዎች የተሰበሰበውን ድምፅ የመደመር ስራ እየተሰራ ነው – ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በአብዛኛው የምርጫ ክልሎች ከጣቢያዎች የተሰበሰበውን ድምፅ የመደመር ስራ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ተናገሩ።
ሰብሳቢዋ በ6ኛው ሃገራዊ ምርጫ አጠቃላይ ሂደት ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸው በአማራ ክልል ድል ይብዛ 11 ምርጫ ጣቢያዎች እንዲሁም በአፋር ደሎን የምርጫ ክልል ከጣቢያ ወደ ምርጫ ክልል አልደረሰም ብለዋል።
በተጨማሪም በሲዳማ አርቤጎና የተወሰኑ ምርጫ ጣቢያዎች ወደ ምርጫ ክልል አለመድረሳቸውንም ገልጸዋል፡፡
በተወሰኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ የምርጫ ክልሎች ውጤት ይፋ መደረጉንም አክለዋል።
በምርጫ ህጉ መሰረት ድምፅ በተሰጠ በአምስት ቀናት ውስጥ በምርጫ ክልል ደረጃ ውጤት እንዲገለፅ ይጠበቃል ያሉት ሰብሳቢዋ፥ ሁሉም በተያዘው ቀን እንዲገልፁ ድጋፍ በመደረግ ላይ መሆኑንም ተናግረዋል።
አሁን ላይም 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የውጤት ማጠቃለያ ስራ እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰው፥ ብዙዎቹ ውጤቶች እየደረሱ መሆኑን አውስተዋል።
ውጤቶቹ ጊዜያዊ መሆናቸውን አመላክተው፥ የምርጫ ክልሎቹ ውጤትን ለማሳወቅ ሁለት ቀናት መቅረታቸውንም አስረድተዋል፡፡
ውጤት ካጠቃለሉና ይፋ ካደረጉት መካከልም በአዲስ አበባ የምርጫ ክልል 15 ሙሉ ውጤቱን ጨርሶ አቅርቧል ነው ያሉት።
የምርጫ ታዛቢዎችም ሪፖርታቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ገልፀው ይህም የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።
በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሀገር በቀል ታዛቢዎች ተሳትፏቸው የላቀ እንደነበርም አውስተዋል።
በየቦታው የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚያጋጥማቸውን ችግር ለመፍታት ዴስክ ተዘጋጅቶ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
ፓርቲዎች ብዙ ቅሬታዎች ቀርበዋል ፣አንዳንዶቹ በጥልቀት የሚመረመሩ ናቸው፡፡
ሌሎቹ ደግሞ በምርጫው ጥራት ላይ የሚፈጥሩት ችግር የሌላቸው ናቸው በኛ ደረጃ የሚታዩትን እናያለን ብለዋል።
በታዛቢዎች የቀረቡ ሪፖርቶች ገንቢዎች የነበሩ ናቸው ያሉ ሲሆን አንዳንዶቹ ግን ዝርዝር ጉዳዮችን አላቀረቡም ብለዋል።
የቀረቡ አቤቱታዎችን ቦርዱ ይመረምራል ያሉ ሲሆን አልፎ አልፎ ጣቢያዎችንና ውሱን ቦታዎችን ያልገለፁ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።
ከፊል አቤቱታዎች ምርጫ ቦርድን የሚመለከቱ አለመሆናቸውንም ጠቁመዋል።

በኦሮሚያ ክልል ነገሌ ግድፈት ተፈፅሟል። ምርጫ ክልሉ በህትመት ችግር ምርጫ እንዳይካሄድ ቢወሰንም በምርጫ ክልሉ 100 የምርጫ ጣቢያች ድምፅ ተሰጥቷል ነው ያሉት።

ድምፁ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ይሆናል ያሉት ሃላፊዋ የቦርዱን ውሳኔ ችላ በማለት ድምፅ ያሰጡት በህግ ይጠየቃሉም ነው ያሉት

አሁን ከውጤት ጋር የተያያዙ አቤቱታዎችን እየፈታን ነው ብለዋል።

ከኢዜማ በኩል ለምርጫ ቦርድ በደብዳቤ የቀረበ አቤቱታ የለም፣ ሆኖም ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ቦርዱ ይሰራል ነው ያሉት።
ከእናት ፓርቲ እስቴ 3 ላይ ቅሬታ ቀርቦ ነበር፣ ቦርዱ አጣርቷል ያሉ ሲሆን÷ተያዘ የተባለው አባልም ከእስር ተፈቷል ሲሉ ገልጸዋል።
ወደ ውጤት ቋት የማይገቡ ሁለት የምርጫ ጣቢያዎች አሉ ያሉ ሲሆን÷ ቦታዎቹም 24 እና ንፋስ ስልክ የሚገኙ ናቸው።
ከተመዘገቡት ድምፅ የሰጡት ሰዎች ወደፊት ይፋ የሚደረግ ሆኖ አብዛኛው መራጮች ግን ድምፃቸው አልባከነም ብለዋል።
በአፈወርቅ እያዩና ለይኩን ዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
384
Engagements
Boost Post
590
8 Comments
20 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.