Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እና ሀብት ሳተላይት ለማምጠቅ የተለያዩ መስረተ ልማቶችን ለሟሟላት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እና ሀብት ሳተላይት ለማምጠቅ የተለያዩ መስረተ ልማቶችን ለሟሟላት እየተሰራ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ምክትል ዋና ዳሬክተር ዶክተር የሺሁን አለማየሁ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ የስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ በሀገር አቀፍ ደረጃ በርካታ የብሔራዊ ጥቅም አገልግሎት ይኖረዋል፡፡
 
በተለይም ለግብርና ለደህንነት እንዲሁም ለሌሎች አገልግሎቶች ከፍተኛ ፋይዳ አለው።

በሌላም በኩል ተቋሙን ለመስህብነትና የሚጎበኝ ቦታ ለማድረግ በአዲስ መልክ በማደራጀት ስራዎች እተየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያም የራሷ ሳተላይት እንዲኖራት ጥናት በማጥናት በፕላን ኮሚሽን ተቀባይነት አግኝቶ ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅት ተደርጓልም ነው ያሉት።

የተቋሙን የሰው ኃይል ጨምሮ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት ወደፊት ለበርካታ የሰው ሀይል የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ ነው ብለዋል ።

በቀጣይም ሶስተኛውን ሳተላይት በኢትዮጵያውያን እውቀት እና ሀብት ለማምጠቅ ጥናት እና ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን መሆኑን ገልፀዋል።

የስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ የግሉም ባለሀብት ወደ ስራው ገብቶ መዕዋለ ነዋዩን እንዲያፈስ ጥሪ አቅርበዋል ።

በሲሳይ ጌትነት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.