Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በህዳሴ ግድብ የመረጃ ልውውጥ ላይ ትኩረት ባደረገ ስብሰባ ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መረጃ ልውውጥ ላይ ትኩረቱን ባደረገ ስብሰባ ላይ ተሳተፉ፡፡

በበይነ መረብ የተካሄደው ስብሰባ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት እና የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀ መንበር ፌሊክስ ሺሴኬዲ የተዘጋጀ ሲሆን፥ በህዳሴ ግድብ ላይ መረጃ መለዋወጥን አላማው ያደረገ ነው፡፡

ሊቀ መንበሩ በዚህ ወቅት የአፍሪካ ጉዳዮች በህብረቱ ስር እንደሚቆዩ ጠቅሰው፥ ሁሉም አካላት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የሚያደርጉትን ድርድር መቀጠል ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

በስብሰባው ላይ ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ቲሼኬዲ ጉዳዩን አስመልክቶ በተገቢው ሰዓት ሙሉ ሪፖርቱን እንደሚያቀርቡ እና ውይይቱ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የአፍሪካ ጉዳይ በአፍሪካ ህብረት በኩል ሊፈታ እንደሚገባ ሊቀመንበሩ እንዳሰመሩበትም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የትዊተር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.