Fana: At a Speed of Life!

የህዝብን ድምፅ የበላይነት አክብሮ እንደሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ዴሞክራሲ ለሀገሪቱ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ የህዝብ ድምፅ የበላይነትን አክብሮ እንደሚንቀሳቀስ በሲዳማ ክልል 12 የፖለቲካ ፖርቲዎች በአባልነት የያዘው የጋራ ምክር ቤት አስታውቋል።
የጋራ ምክር ቤቱ 6ኛው ጠቅላላ ምርጫን አስመልክቶ በሀዋሳ ከተማ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት የምክር ቤቱ ፀሐፊ አቶ ታምራት አሰፋ እንዳስታወቁት፥ ምርጫው በክልሉ የነበረው ሂደት ከዕጩዎች ምዝገባ አንስቶ እስከ ምርጫው መጠናቀቅ ድረስ ሰላማዊ ሆኖ ተጠናቋል።
ሂደቱ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የክልሉ ህዝብ ላደረገው አስተዋፅኦ እና ጨዋነት የተሞላበት አካሄድ ምክር ቤቱ አክብሮቱን ገልጿል።
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩ ተወዳዳሪዎች ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ በማድረግ ሀገርና ህዝብን በማሻገር ሂደት ለተጫወቱት ሚና ምክር ቤቱ አክብሮቱን ይገልጻል ነው ያለው።
በተለይ ዴሞክራሲ ለሀገሪቱ የምርጫ ብቻ ሳይሆን የህልውናና ቀጣይነት የማረጋገጥ ጉዳይ በመሆኑ የጋራ ምክር ቤቱ የህዝብን ድምፅ የበላይነት አክብሮ እንደሚንቀሳቀስ ገልጸው፥ በምርጫው ውጤት ሁሉም ፓርቲዎች ደስ ሊሰኙ ይገባል ብለዋል።
ለምርጫው ስኬታማነት አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉም አካላት ምክር ቤቱ ምስጋና አቅርቧል።
በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የምክር ቤቱ አባላት መካከል ኢሶዴፓ ፣ ኢህአፓ፣ ሲአፓ እና ብልጽግና እንደሚገኙበት የዘገበው ኢዜአ ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.