Fana: At a Speed of Life!

የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ኢትዮጵያን በተለያዩ መስኮች ከፍ እንድትል ያደርጋል-ምሁራን

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ኢትዮጵያን በተለያዩ ዘርፎች ከፍ እንድትል የሚያስችላት መሆኑን የውሃ ጉዳይ ተመራማሪና የምጣኔ ሃብት ምሁራን ገለጹ፡፡

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና የውሃ ጉዳዮች ተመራማሪው ዶክተር ውብእግዜር ፈረደ እንደሚሉት÷ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ወደ ስራ መግባት አዲስ የታሪክ ምዕራፍን የሚከፍት ነው፡፡

ኢትዮጵያ በቀጠናው ጂኦ-ፖለቲካ ያላትን ተደማጭነት በማሳደግ ረገድ ያለው ሚና ከፍ እንደሚልም ነው ተመራማሪው የጠቆሙት፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የምጣኔ ሃብት ባለሙያ እንዲሁም የሶሾ-ኢኮኖሚ ጉዳዮች ተንታኙ አቶ ዋሲሁን በላይ በበኩላቸው÷ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ማነቆ ለሆነው የሃይል አቅርቦት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ይዞት የሚመጣው ትሩፋት ከፍ ያለ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በቂ የሆነ የሃይል አቅርቦትም አዳዲስ የቢዝነስ ዘርፎች እንዲተዋወቁ በማድረግ ረገድ የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሚሆን አንስተዋል፡፡

የፕሮጀክቱ እውን መሆን ሌሎች አቅሞችን በማሳደግ ተጨማሪ ሃገራዊ ፕሮጀክቶችን እውን ለማድረግ እንደሚያግዝም ምሁራኑ አስረድተዋል፡፡

ታላቁ የህዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ ብሎም አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለመገንባትም አንድነትን ማጠናከር እና የተጀመሩ የትብብር ስራዎችን ማነቃቃት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል፡፡

በአወል አበራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.