Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አርማውን ቀየረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በተለያዩ ምክንያቶች አርማ መቀየሩን ይፋ አድርጓል፡፡

አርማውን ለመቀየር በርካታ ምክንያቶች መኖራቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የሰው ኃይል አስተዳደር ምክትል ዘርፍ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ታምራት ዳባ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በሁለንተናዊ የለውጥ ጎዳና ላይ የምትገኝ በመሆኑና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንም ከዚህ ለውጥ ውጪ ባለመሆኑ አርማውን ወቅታዊ ማድረግ እና የለውጡን ሐሳቦች አመልካች እንዲሆን አድርጎ ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑ ከምክንያቶቹ አንዱ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የቀድሞው አርማ አሁናዊ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የሰነቀውን ራዕይ እና ተልዕኮ እንዲሁም ኮሚሽኑ ዛሬ የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ የማይገልፅ መሆኑ ደግሞ ሌላኛው ምክንያት ነው።

የቀድሞው አርማ ከረዥም ዓመታት በፊት የግራፊክስ መሣሪያዎች ባልዘመኑበት ጊዜ የተሠራ አርማ በመሆኑ፣ የጥራት ጉድለቶችም የሚታይበት እንደነበር ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኮሚሽኑ በአዲስ መልክ ያወጣቸውን እሴቶች በቀድሞው እሴት ውስጥ ለማግኘት የሚያስችል አለመሆኑ እና በሰው አዕምሮ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሲፈጥር የቆየ በመሆኑ በቀላሉ የሚጨበጥ እና የሚታወስ እንዳልነበረም ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም የቀድሞው የፖሊስ አርማ ፌዴራል ፖሊስ በአሁን ሰዓት ቀይሮ ሥራ ላይ ካዋለው አርማ የተለየ በመሆኑ እና ፖሊስ አሁን በዘመኑ ከተደረሰበት ዓለም አቀፍ የፖሊስ ስታንዳርዶች ጋር ያስተሳሰረ አለመሆኑ አርማውን መቀየር አስፈልጓል ነው የተባለው፡፡

አዲሱ አርማ አዲሱ አርማ ከሐምሌ 1 ቀን 2013 ጀምሮ በክልሉ ተፈፃሚ እንደሚሆን እና አዲሱን አርማ ከቀድሞው ጋር ጎን ለጎን መጠቀም የሚቻለው ለ6 ወር ብቻ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.