Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ ሱዳን የናይል ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት ማቀዷን ገለጸች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ ሱዳን የናይል ወንዝን በመጠቀም የሀይል ማመንጫ ግድብ ለመገንባት ዕቅድ ማዘጋጀቷን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴንግ ዳው ዴንግ ማሌክ ለናሽናል ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ከዕርስ በርስ ጦርንት የተላቀቀችው ደቡብ ሱዳን ወደ ኢንዱስትሪ መር የገበያ ስርዓት ለመሸጋገር የሚያስችል ሀይል ማመንጫ ግድብ ለመገንባት የሚስችል ገንዘብ አላት።
የግድብ ግንባታ ፕሮጀክቱ መንግስት ከነዳጅ ሽያጭ በሚያገኘው ገቢ ለመገንባት ዕቅድ ከተያዙ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ደቡብ ሱዳን ርካሽ፣ ታዳሽ እና በሀገሪቱ በየጊዜው የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ መከላከል የሚያስችል የግዙፍ ግድብ ግንባታን በይፋ ለማስጀመር ዕቅድ መያዟን ተናግረዋል፡፡
ደቡብ ሱዳን በየወቅቱ በሚፈጠር የጎርፍ አደጋ፣ በሀይል እጥረት፣ የውሃ እጥረት እና በደካማ የመሰረተ-ልማት ችግር እንደምትሰቃይ ጠቅሰዋል።
ወደ ኢንዱስትሪ መሸጋገር የሚቻለው በቅድሚያ የሀይል አቅርቦት አስተማማኝ በሆነ መልኩ ማምረት ሲቻል እንደሆነ እና ግድቡ የሀይል ፍላጎትን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
ግድቡ ምን ያህል ርዝመት፣ ምን ያህል ውሃ መያዝ እና ምን ያህል ሀይል የሚያመነጩ ተርባይኖች ሊኖሩት እንደሚገባ የሚሳይ መነሻ ዝርዝር ዕቅድ እና ጥናት በሀገሪቱ የመስኖ ሚኒስቴር በኩል መከናወኑ በዘገባው ተመላክቷል፡፡
ደቡብ ሱዳን ይህን ግድብ የመገንባት ሉዓላዊ መብት እንዳላት ምክትል ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እየገነባች ባለችው ግዙፍ ግድብ ምክንያት የሚነሱ አለመግባባቶች በትብብር መንፈስና በውይይት መፈታት እንዳለባቸው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.