Fana: At a Speed of Life!

በሁለት ኢትዮጵያን እና አንዲት ስፔናዊት የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢዎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ

 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የህወሃት ርዝራዥ በሚንቀሳቀስበት አካባቢ የሰብዓዊ ድጋፍ በሚያደርጉ ሁለት ኢትዮጵያን እና አንድ ስፔናዊት ላይ ጥቃት ፈፀመ ።

አቢ አዲ በተባለ ስፍራ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን ሰራተኛ በሆኑ ሰዎች ላይ በአሸባሪዉ ሀይል ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።

በዚህም መንግስት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን ይመኛል ብሏል የውጭጉዳይ ሚንስቴር በመግለጫው።

በዚህ አጋጣሚ መንግስት በተደጋጋሚ ለጋሽ እና እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች የፀጥታ ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች ላይ ለሰራተኞች ደህንነት ሲባል ማንኛውም እንቅስቃሴ በመከላከያና በፀጥታ አካላት ታጅበው ለዜጎች እንዲያደርሱ ሲመክር መቆየቱ ይታወሳል ።

ይሁን እንጅ አልፏ አልፏ የተወሰኑ ሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶቾ ከመንግስት እውቅና ውጪ ሲንቀሳቀሱ ይስታዋላል ይህም የከፈ ችግር እያስከተለ ነው።

ውሉ ባልታወቀ አላማ የንፁሃን ሞት ዛሬም የፖለቲካ ትርፍ ለማግኝት የሚሯሯጠው የአሸባሪው የተበታተኑ ሽፍቶችን ለህግ ለማቅረብ መንግስት ዛሬም ህዘባዊነቱን ጠብቆ ለዜጎች ሰላም እና ለአገራችን ሉዐላዊነት ይሰራል ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.