Fana: At a Speed of Life!

ሳኡዲ አረቢያ የነበሩ ዜጎችን ወደ አገር  የመመለስ ሥራ ተጀምረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በዛሬው ዕለት በ6 በረራ  ሳኡዲ አረቢያ የነበሩ ዜጎችን ወደ አገር  የመመለስ ሥራ መጀመሩን ሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

መንግስት ከሳኡዲ አረቢያ መንግስት ጋር በመሆን በቅንጅት በሳኡዲ አረቢያ በተለያዩ ማቆያ ማእከላት ውስጥ የሚገኙ ቁጥራቸው 40 ሺህ የሚጠጉ ዜጎችን በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ በተከታታይ ወደ አገር የመመለስ ሥራውን ዛሬ ጀምሯል።

በዚህ የማስመለስ ሥራ ቅድሚያ ወደ አገር እንዲገቡ የተደረጉት ሴቶች፣ ህጻናት እና ታማሚ ኢትዮጵያውያን ዜጎች መሆናቸው ተመላክቷል።

ይህ ዜጎችን ወደ አገር የመመለስ ዘመቻ በታቀደው ጊዜ ይሳካና ይጠናቀቅ ዘንድ የአገራችን ልዑካን ቡድን አባላት፣ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ በጂዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈትቤት እንዲሁም በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በጎ ፈቃደኛ ግለሰቦች ተካተውበት ከሚመለከተው የሳዑዲ አረቢያ ወገን ጋር በቅንጅት እየሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ይህ የአሁኑ ዜጎችን ወደ አገር የመመለስ ሥራ የሚመለከተው የሳኡዲ አረቢያን ድንበር ደህንነት ሥርዓት ጥሰው የገቡ፣ የአገሪቱን የመኖሪያ ፍቃድ እና የሥራ ፈቃድ ህግጋትን ተላልፈው በተለያዩ ማቆያ ጣቢያዎች የሚገኙ ዜጎችን ነውም ተብሏል።

ይህም ዜጎች የማስመለስ ተግባር የዜጎችን ሰብዓዊ ክብር በጠበቀና በራሳቸው ፍቃድእንዲሁም በሁለቱ አገራት መንግስታት የጋራ ትብብር እየተከወነ የሚገኝ መሆኑን ሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.