Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ መልክ የተዋቀረውን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ መርቀው ከፍተዋል ።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለከፍተኛ አመራሩ የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚሰጥበት ነው ተብሏል።

አካዳሚው ከሀገር ተሻግሮ ለመላው አፍሪካ የሚያገለግልም  መሆኑም ተገልጿል።

የአካዳሚው አዲሱ ግንባታ በ2011 ዓ.ም መጋቢት ወር ላይ ተጀምሮ በፍጥነት እና በጥራት መጠናቀቁም ነው የተገለጸው  ።

አካዳሚው በሱሉልታ ከተማ በአርባ ሄክታር መሬት ላይ የተገነባ  መሆኑ ተመላክቷል።

አጠቃላይ የግንባታ ወጪውም 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ነው።

ከዚህ ውስጥ 722 ሚሊየኑ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ሲሆን ቀሪው የቻይና መንግስት ድጋፍ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.