Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካን ችግር መቅረፊያ ትልቁ  መንገድ   እውቀት ነው -ጠ/ ሚ ዐቢይ አህመድ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድየአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ የኢትዮጵያን ብሎም ተሻግሮ የአህጉሪቱን ችግር በእውቀት ለመፍታት የተመሰረተ ነውም ሲሉ ገልጸዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ÷ አፍሪካ ሁል ጊዜ የሌሎችን ሀሳብ ብቻ ተቀባይ መሆኗ የድህነት ተምሳሌት አድርጓት ቆይቷል ብለዋል።

ሆኖም አህጉሪቱ የብዙ እውቀቶች እና ባህሎች ባለቤት በመሆኗ ይህን ማጎልበት ይገባል ብለዋል።

አካዳሚው የአመራር እውቀት ብቻ ሳይሆን ክህሎት የሚፈልቅበት ይሆናል ተብሏል ።

በአካዳሚው ከመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተጨማሪ ለቢዝነስ ሰዎች ፣ለዲፕሎማቶች ስልጠና ይሰጥበታል።

በዓላዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.