Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል የሚስተዋለውን የኤች አይ ቪ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችል ንቅናቄ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል የሚስተዋለውን የኤች አይ ቪ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችል ንቅናቄ በይፋ ተጀመረ።
ባለፉት 30 ዓመታት ብዙዎችን ለህመምና ለሞት በመዳረግ በማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና በስነ ልቦና ላይ ከፍተኛ ጫና እያስከተለ ያለው የኤች አይ ቪ/ኤድስ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ህብረተሰቡ መዘናጋት ውሰጥ መግባቱን ተከትሎ የስርጭት አድማሱን እያሰፋ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
አሁን ላይ በሀረሪ ክልል የበሽታው ስርጭት 2ነጥብ 9 በመሆን በሃገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የስርጭት መጠን ካለባቸው በአራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑ ተመላክቷል።
ይህንን ለመቀየርና የስርጭት ሁኔታውንም በመቀነስ ህብረተሰቡ ከበሽታው እንዲጠበቅ ህዝባዊ የንቅናቄ መድረክ ማዘጋጀት ማስፈለጉን የሀረሪ ክልል የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጫላ መሐመድ ተናግረዋል።
አያይዘውም ሃገሪቱ የጀመረችው የብልፅግና ጉዞ በወጣቱ ትውልድ የሚረጋገጥ በመሆኑና በሽታው ወጣቱን እያጠቃ በመሆኑ አምራቹን ኃይል ከዚህ በሽታ በመጠበቅ የሃገሪቱን እድገት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።
የንቅናቄ መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ÷ ለኤች አይ ቪ ኤድስ ከዚህ በፊት ይሰጥ የነበረው ትኩረት በመቀነሱ ሳቢያ ከጊዜ ወደ ጊዜ የስርጭት መጠኑ መጨመር ማሳየቱን ተናግረዋል።
በዚህም በ2012 በሀረሪ ክልል በተደረገ ምርመራ 328 አዳዲስ በበሽታው የተያዙ ሠዎች መገኘታቸውን አመልክተዋል።
የሚስተዋለው መዘናጋት ከዚህ የበለጠ ዋጋ ሳያስከፍለን በሽታውን ከመከላከል አኳያ ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የሚጠበቅ ኃላፊነት ያሉት ወይዘሮ ሚስራ÷ በተለይም የሃይማኖት አባቶች፣አባገዳዎችና የሃገር ሽማግሌዎች መታቀብንና ራስን መጠበቅ ላይ ትምህርት እንዲያስተምሩ አደራ ብለዋል።
በተሾመ ኃይሉ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
2
Engagements
Boost Post
1
1 Comment
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.