Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ በአሸባሪው ህወሃት ቡድን በሰብዓዊ ድጋፍ  ሰጪ ሰራተኞች ላይ የተፈጸመውን  ጥቃት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ የሰብዓዊ ድጋፍ በሚሰጡ ዜጎች ላይ በአሸባሪው ሕወሃት ርዝራዥ በደረሰው ጥቃት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ ÷ የህወሃት አሸባሪ ርዝራዥ ቡድን ሰብዓዊ ዕርዳታ ሲሰጡ የነበሩ ንጹሃንን ላይ ጥቃት መፈጸሙ ጊዜውን የማይመጥን እኩይ ተግባር ነው ብለዋል።

በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚያደርሰው መሰል ጥቃት የቡድኑን ተስፋ የቆረጠ እንቅስቃሴ ያሳየ ነውም ብለዋል።

በቡድኑ ጥቃት የደረሰባቸው ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን አባላት በሆኑት አስተባበሪያዋ ማሪያ ሀርናንዴዝ፣ ረዳት አስተባባሪ የነበረው ዮሃንስ ሀለፎም የድርጅቱ አሽከርካሪ ቴድሮስ ገብረማሪያም መገደላቸውን ገልጾ÷ ይህን እኩይ ተግባር መላው ህብረተሰብ እንዲያወግዘው ጥሪ አቅርቧል።

በክልሉ ለሚደረገው የሰብዓዊ ድጋፍ አሰጣጥ የጸጥታ ጉዳይ በተመለከተ ከፌዴራልና ከክልል የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ÷ በጥቃቱ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸው ÷ ለሟች ቤተሰቦች፣ ጓደኞችና በኢትዮጵያ ለሚቀንሳቀሱ ድንበር የለሽ የሀኮሞች ቡድን መጽናናትን መመኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.