Fana: At a Speed of Life!

750 ሚሊየን ብር ወጪ የሚደረግበት የጅግጅጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅግጅጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ በይፋ ተጀመረ፡፡

በ750 ሚሊየን ብር የሚገነባው ሁለተኛው ዙር የጅግጅጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ሥራ በቻይናው የሲቪል ስራ ኮንስትራክሽን ድርጅት ከናወን ሲሆን፥ ግንባታው በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።

የፕሮጀክቱ ወጪ ሙሉ በሙሉ በሶማሌ ክልል የሚሸፈን ሲሆን፥ ሲጠናቀቅ 264 ሺህ 356 የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የክልሉ ውሃ ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱረህማን አህመድ ፕሮጀክቱ ላለፉት 10አመታት ይሰራል ተብሎ የባከነ እንደነበር መናገራቸውን የሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን መረጃ ያመላክታል፡፡

ጅግጅጋ ከተማ በአሁኑ ወቅት 9 ሺህ 745 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃን በቀን የምታገኝ ሲሆን የፕሮጀክቱ መጠናቀቅ የከተማዋን የንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ያሳድጋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.