Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የተለያዩ አዋጆችንና ለፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ከ630 ሚሊየን ብር በላይ በጀት በማጽደቅ ጉባዔውን አጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ምክር ቤት 3ኛ አስቸኳይ ጉባዔውን ለፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ከ630 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀትና የተለያዩ አዋጆችን በማጽደቅ ዛሬ አጠናቀቀ።

የክልሉ ምክር ቤት ትናንት የተጀመረው ጉባኤ በበጀት አመቱ በክልሉ ለተከናወኑ መደበኛና ካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ 630 ሚሊየን 241 ሺህ 375 ብር ተጨማሪ በጀት በማጽደቅ ዛሬ አጠናቋል።

ምክር ቤቱ በተጨማሪም የተለያዩ የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ሃላፊነት ለመደንገግ የወጡ ሶስት ተጨማሪ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ማጽደቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በምክር ቤቱ ከጸደቁት አዋጆች መካከል በክልሉ ሀብትን ለማሳወቅና ለማስመዝገብ የተዘጋጀው አዋጅና የክልሉን የልማት ድርጅቶች አመሠራረት፣ አደረጃጀት፣ አመራርና ድጋፍ አሠጣጥን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ይገኙበታል።

ምክር ቤቱ በአዋጆቹ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ስራ ላይ እንዲዉሉ በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ጉባኤውን አጠናቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.