Fana: At a Speed of Life!

በደሴ ከተማ አንዲት እናት ሶስት ወንድ ልጆችን በአንዴ ተገላገለች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ አንዲት እናት ሶስት ወንድ ልጆችን በአንዴ ተገላገለች።

ወይዘሮ ራቢያ ሸምሰዲን በትላንትናው ዕለት ነው ሶስት ወንድ ልጆችን የተገላገለችው።

በደሴ ከተማ ሮቢት ሰፈር ነዋሪ የሆነችው ወይዘሮ ራቢያ የምጥ ስሜት ስለተሰማት ወደ ሆስፒታል ታመራለች፡፡

ሆስፒታል እንደደረሰችም አምጣ መውለድ ስለማትችል በቀዶ ጥገና ልጆቿን እንድትወልድ በጤና ባለሙያ ይነገራታል፡፡

በዚህ መሠረትም ወይዘሮ ራበያ ሶሰት ወንድ ልጆችን በአንዴ በሰላም ተገላግላለች።

ወይዘሮ ራቢያ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራት ቆይታም ÷ በአንድ ጊዜ ሶስት ልጆችን በማግኘቴ ደስታ ተሰምቶኛል ብላለች።

ባለቤቷ አቶ ኑሩ መሃመድ በበኩላቸው አሁን ላይ ሶስቱም ልጆች በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በከድር መሀመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.