Fana: At a Speed of Life!

የፖለቲካ ፓርቲዎች በሃገራዊና ክልላዊ ልማት ላይ የጀመሩትን ተሳትፎ አጠናክረው መቀጠል አለባቸው-አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፖለቲካ ፓርቲዎች በሃገራዊና ክልላዊ ልማት ላይ የጀመሩትን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ጠየቁ።

በጋምቤላ ክልል የሚንቀሳቀሱ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ሃገራዊና ክልላዊ ልማት ላይ የጀመሩትን ተሳትፎ እንዲያጠናክሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ፓርዎቹ በጋራ የአረንጓዴ አሸራ ችግኝ ተከላ መረሃ ግብር ዛሬ ከስዓት በኋላ በጋምቤላ ከተማ አካሒደዋል።

አሁን በመንግስት እየተካሄደ ለሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ ልማትና ሌሎች ሀገራዊ የልማት አጀንዳዎች ስኬት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባም አቶ ኡሞድ አስገንዝበዋል።

ስድስተኛው ሀገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ፓርቲዎቹ ለነበራቸው ተሳትፎም ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም ለህዝብና ለሀገር ብሔራዊ ጥቅም ስኬት ፓርቲዎቹ የጀመሩትን ተሳትፎ አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳደሩ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የጋምቤላ ህዝቦች ፍትህ ሰላም ልማት ዴሞክራሲ ንቅናቄ /ጋህፍሰልዴን/ ተወካይ አቶ ላም ኒያል በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንደበር ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.