Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በ2014 ዓ.ም 906 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የምግብ ዘይት ፍጆታ እንደሚኖራት ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን የምግብ ዘይት ፍጆታ በሀገር በቀል አምራች ኢንዱስትሪዎች ለመሸፈን በሚደረገው ጥረት በገጠሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ኡመር ሁሴንን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ሀገር በቀል የምግብ ዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎች ተገኝተዋል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ውስጥም የሀገር ቤት ፍጆታን በሀገር ውስጥ አቅም የመተካት እቅድ አንዱ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ ÷ ይህም የዜጎችን የኑሮ ጫና በመቀነስ የኑሮ ውድነትን ያቃልላል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በመጭው 2014 ዓ.ም 906 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የምግብ ዘይት ፍጆታ ይኖራታል ተብሎ እንደሚጠበቅም አቶ መላኩ ጠቁመዋል።

ለዚህ ፍላጎትም በሀገር ቤት ያሉ ኢንዱስትሪዎች 1 ነጥብ 25 ቢሊየን ሜትሪክ ቶን የማምረት አቅም ላይ መድረሳቸውን አንስተዋል።

ይሁን እንጂ ኢንዱስትሪዎቹ ባሉባቸው በርካታ ተግዳሮቶች ምክንያት በሙሉ አቅማቸው እየሰሩ አለመሆኑን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

በሀገሪቱ 232 የምግብ ዘይት ኢንዱስትሪዎች የሚገኙ ሲሆን÷ከእነዚህ ውስጥም 26 ያህሉ መካከለኛና ከፍተኛ፣ 206 ያህሉ ደግሞ አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ናቸው።

በአፈወርቅ እያዩና ትዝታ ደሳለኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!እስከ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.