Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መስጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ለ2013 የትምህርት ዘመን ለ8ኛ ክፍል ፈተና ሲደረግ የነበረው ቅደመ ዝግጅት ተጠናቆ በዛሬው እለት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ፈተናው መሰጠት ተጀምሯል።

በክልሉ ዛሬ በተጀመረው የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ735 የፈተና መስጫ ማእከላት 44 ሺህ 144 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሏል።

የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አብዲቃድር መሀመድ÷ በጅግጅጋ ከተማ በሚገኘው የዊልዋል አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የ8ኛ ክፍል ፈተናን አስጀምረዋል።

አቶ አብዲቃድር መሀመድ በወቅቱም÷ በክልሉ የ2013 አመት የ8ኛ ክፍል በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ዛሬ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች መጀመሩን ገልፀዋል።

አያይዘውም አህመድ ጉሬ ትምህርት ቤት እና በጅግጅጋ ከተማ ማረሚያ ቤት የፈተናውን አሰጣጥ ሂደት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በክልሉ የተጀመረው የ8ኛ ክፍል ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት እንዲወጡም አሳስበዋል።

በሶማሌ ክልል ዛሬ የተጀመረው የ8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 23 እንደሚጠናቀቅ ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.