Fana: At a Speed of Life!

በሸካ ዞን ከቀያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደቀያቸው እየተመለሱ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ሸካ ዞን ተፈጥረው በነበሩ ግጭቶች ከቀያቸው የተፈናቀሉ የአካባቢ ነዋሪዎች ወደቀያቸው እየተመለሱ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በዞኑ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጥረው በነበሩ ግጭቶች ከቀያቸው የተፈናቀሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ተግባር በክልሉ እና በዞኑ ድጋፍ እንዲሁም በአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፎ ተፈናቅለው ከነበሩት 11 ሺህ 78 ዜጎች መካከል 6 ሺህ 742 ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስ እንደተቻለ ተገልጿል፡፡
ወደ ቀያቸው ለተመለሱት ተፈናቃዮች አዲስ 113 የሳር ክዳን ቤቶች ፣ 75 የቆርቆሮ ክዳን ቤቶች እና በከፊል የወደሙ 218 ቤቶች ጥገና በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የተቀሩትን ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ለመመለስ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር ድጋፍና ክትትል ቡድን የገለፀ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎችም ሚኒስቴሩ እያደረገ ያለውን የድጋፍና ክትትል ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.