Fana: At a Speed of Life!

የ8ኛ ክፍል ፈተናን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአማራ ክልል ት/ት ቢሮ ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 እስከ 25ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የፈተናው ወረቀት መድረሱን በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ባለሙያና ተወካይ ቡድን መሪ አቶ ሃይሉ ታምር ጠቁመዋል።

ፈተናው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ በየደረጃው ያሉ የጸጥታ አካላት እየሠሩ እንደሚገኝ ተወካይ ቡድን መሪው ተናግረዋል።

አቶ ኀይሉ እንዳሉት ተማሪዎች ለፈተናው ዝግጁ እንዲኾኑ መሸፈን የሚገባቸው የትምህርት ይዘቶች እንዲሸፈኑ ሰፊ ሥራ ሲሠራ ቆይቷል።

ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ በየደረጃው ለተቋቋመው ግብረ ኀይል በቂ የሥራ መመሪያ እየተሰጠ መሆኑን ገለጹት አቶ ሃይሉ÷ኀላፊነት የተሰጣቸው አካላትም ኀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በነገው ዕለት ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና አሰጣጥ መመሪያ ስለሚሰጥ ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች ተገኝተው እንዲከታተሉ አቶ ሃይሉ አሳስበዋል።

ከሰኔ 23 እስከ 25/2013 ዓ.ም በሚሰጠው ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና 412 ሺህ 497 ተማሪዎች ለፈተና የሚቀመጡ ሲሆን÷5 ሺህ 521 ትምህር ቤቶች ደግሞ ፈተናውን እንደሚሰጡ ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.