Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ ኢትዮጵያ በአብዬ ግዛት ባላት ተልዕኮ ዙሪያ ከተመድ የስራ ሃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተመድ የምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካ፣ የሰላም ግንባታ ጉዳዮች እና ዘመቻ መምሪያ ዳይሬክተር ግርሃም ሜይትላንድ ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱ በአብዬ ግዛት የሚገኘውን የተመድ ጊዜያዊ ሰላም አስከባሪ ሃይል ስትራቴጂክ ግምገማና ተልዕኮውን በድጋሚ ማዋቀር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህ ወቅት አቶ ደመቀ ሰላም አስከባሪ ሃይሉ በአብየ ግዛት መቆየት እንዳለበት አቅሰው፥ ተልዕኮውን እንዲወጣ አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግለት እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የሰላም አስከባሪ ሃይሉ ከስፍራው መውጣት በአካባቢው ያለውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋትና ግጭት ያባብሰዋልም ነው ያሉት፡፡

ሱዳን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር ከአብዬ ግዛት ለቆ እንዲወጣ ካቀረበችው ጥያቄ ጋር ተያይዞም፥ ሰላም አስከባሪ ሃይሉ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በደረሱት ስምምነት መሰረት በተመድ ስር በስፍራው መሰማራቱን አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም የኢትዮጵያ ወታደሮችም ጦርነትን ለመከላከል ዋጋ መክፈላቸውን አውስተው፥ ለቀው መውጣታቸው አስፈላጊ ከሆነም በባለድርሻ አካላት ስምምነትና መግባባት ተደርሶበትና በአግባቡ ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.