Fana: At a Speed of Life!

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 110 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡
ዩኒቨርሲቲው ለ13ኛ ዙር በዘጠኝ የትምህርት ኮሌጆች በመጀመሪያ ዲግሪና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው ዛሬ ያስመረቀው፡፡
የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ማስመረቁ ተገልጿል፡፡
ዩኒቨርስቲዉ በሶስተኛ ዲግሪ ለሁለተኛ ጊዜ ተማሪዎችን ማስመረቁ በመማር ማስተማር ሂደቱ በፈጣን ለውጥ ላይ መሆኑን የሚያሳይ መሆኑ ተነግሯል።
በምርቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታና ሌሎች ከፍተኛ የትምህርት አመራሮች ተገኝተዋል።
የትምህርት ተቋሙ እስካሁን ከ26 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡
በኤልያስ ሹምዬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.