Fana: At a Speed of Life!

ጀነራል ዊንጌት ትምህርት ቤት በርካታ ፖለቲከኞችን፣ የአገር ባለዉለታዎችንና ሙያተኞችን ያፈራ አንጋፋ ተቋም ነው-ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በጄነራል ዊንጌት ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ለምስራቅ አፍሪካ የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና የልህቀት ማዕከል ግንባታ በዛሬው ዕለት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡

የመሰረት ድንጋዩን ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ጋር በመሆን ማስቀመጣቸው ተገልጿል።

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ  ኮሌጅ በአለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ሽግግር ቀጠናዊ ትስስር ፕሮጀክት መስፈርት በሟሟላቱ በኢነርጂ ዘርፍ የኤልክትሪካል እና ዲጂታል ማዕከል  ከዓለም ባንክ የ557 ሚሊየን ብር  በጀት ተጠቃሚ መሆኑ ተመላክቷል።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ÷ ጀነራል ዊንጌት ትምህርት ቤት በርካታ ፖለቲከኞችን፤ የአገር ባለዉለታዎችንና ሙያተኞችን ያፈራ አንጋፋ ተቋም ነው ብለዋል።

ኮሌጁ ከዚህ በላይ ከፍ እንዲልና በዩኒቨርስቲ ደረጃ እንዲያድግ የከተማ አስተዳደሩ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በጋራ ይሰራልም ነው ያሉት ።

የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት  ለኢትዮጵያ  የብልጽግና ጉዞ መሰረት መሆናቸውን የገለፁት ምክትል ከንቲባዋ ÷የከተማ አስተዳደሩ በቴክኒክ እና ሙያ የሚተጉ እጆችን ያበረታታል በዚህም ከግብዓት ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

ለዚህ የልዕከት ማዕከል እውን እንዲሆን  የአለም ባንክን ጨምሮ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች እና ሌሎች አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላት  ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ በበኩላቸው÷ የፕሮጀክቱ በተለያዩ  የሙያ ዘርፎች ጥራትን ለማሻሻል ፣ተደራሽነትን ለማሳደግ እና አህጉራዊ ግንኙነትን ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል።

የልዕቀት ማዕከሉ መገንባት ከከተማዋ አልፎ ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ በኤነርጂ ዘርፍ እና የኢንዱስትሪ ትስስር በመፍጠር በኩል የተያዘውን እቅድ ለማሳካት እና በገበያው የሚፈለገውን የሰው ሀይል በብዛት በማፍራት በኩል ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ዶክተር ሳሙኤል ተናግረዋል ።

ፕሮጀክቱ ዘመናዊ የአስተዳደር ህንጻን ጨምሮ የተማሪዎች ማደሪያ፤ ቤተ-ሙከራ እና  የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ የላብራቶሪ ማዕከል ያካተተ  መሆኑን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.