Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ከተማ የወባ በሽታን ለመከላከል የሚያስችል 123 ሺህ አጎበር እየተሰራጨ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ከተማ የወባ በሽታን ለመከላከል የሚያስችል 123 ሺህ አጎበር እየተሰራጨ መሆኑን የጅማ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል በ 17ቱም የጅማ ከተማ ቀበሌዎች 123 ሺህ አጎበር ለህብረተሰቡ ማከፋፈል መጀመሩን ነው ፅህፈት ቤቱ የገለጸው፡፡
ከክረምት መግባት ጋር ተያይዞ የወባ በሽታ ስርጭትን ለመቀነስ እና ለማጥፋት ህብረተሰቡ አጎበርን በአግባቡ መጠቅም እንዳለበት በ ጽህፈት ቤቱ የወባ ስርጭት መቆጣጠርና መከላከል ሀላፊ አቶ ሀይሌ ለገሰ ተናግረዋል።
ጽህፈት ቤቱ የ2030 የጤና ግብ ለማሳካት የወባ በሽታ ስርጭትን ለመከላከልና ለማጥፋት የሚያችሉ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ታውቋል።
በወርቃአፈራው ያለው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.