Fana: At a Speed of Life!

የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2013 በጀት ዓመት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በቡታጅራ ከተማ መጀመሩን የሴቶችና ህጻናት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ ወይዘሮ ህይወት ሀይሉ እንደገለፁት፥ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባለፉት 12 ዓመታት ተቋማዊ በሆነ መልኩ በበጋውና በክረምት ወቅት በመደበኛነት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

ዘንድሮም “በወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ኢትዮጵያን እናልብሳት” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ በይፋ መጀመሩን ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ ከ18 ሚሊየን በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ የተገለፀ ሲሆን ወጣቶቹን በ13 የስራ መስኮች በማሰማራት ከ48 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ልዩ ልዩ ተግባራት ለማከናወን ዕቅድ ተይዟል ብለዋል፡፡

በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ በመንግስትና በህዝብ ሊወጣ የሚችል 10 ቢሊየን ብር ሀብትን ለማዳን እቅድ መያዙን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወጣቶቹ ከሚሰማሩባቸው የስራ መስኮች በተጨማሪም እንደሃገር ለሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ስኬታማነት በችግኝ ተከላው እንዲሳተፉ ይደረጋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በሰብዓዊ ድጋፎች፣ የትምህርት ቤቶችና የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች ጥገና፣ ኮቪድን እንዲሁም መጤ ልማዶችን፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርና ፍልሰት ብሎም የትራፊክ አደጋንና ኤች አይ ቪ ኤድስን የመከላከል ተግባራት ላይ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.