Fana: At a Speed of Life!

የፀጥታው ሀይል ባጠረ ጊዜ አሸባሪውን የህውሀት ቡድን ለመደምሰስ ይሰራል – የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የፀጥታው ሀይል ባጠረ ጊዜ አሸባሪውን የህውሀት ቡድን ለመደምሰስ እንደሚሰራ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ተናገሩ፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ከክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች ጋር ልዩ አስቸኳይ ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል።

ውይይቱ ፖሊስ ሀገራዊ ተልዕኮውን ይበልጥ ማገዝ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ ሀገራዊ የወቅታዊ ስምሪቶችን መገምገም እና አቅጣጫ ማስቀመጥ ላይም እየመከረ ነው፡፡

በተለይ በአማራና በአፋር ክልሎች ላይ አሸባሪው ቡድን እያደረገ ያለውን ትንኮሳ የሚታወቅ ሲሆን፥ ባለበት እርምጃ ለመውሰድ እየተሰራ ስላለው ስራ ላይም እየተወያዩ ነው፡፡

በተመሳሳይ አሸባሪ ቡድኑ በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል፣ በደቡብና መሰል አካባቢዎች ላይ ያስታጠቃቸው የጥፋት ሀይሎች ላይ እርምጃ በመውሰድ ዙሪያ እየመከሩ ነው፡፡

በተጨማሪም ቡድኑ ለአመታት የመዘበራቸውን የሀገር ሀብትና ንብረቶች ከማጣራትና ከማስመለስ አንፃር ላለፉት ስምንት ወራት እየተሰራ ባለው ስራ ከ6ነጥብ 5ቢሊየን ብር ግምት ያለው ንብረት ማገድና መቆጣጠር መቻሉ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ከ5ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት የጁንታው የኢኮኖሚ ምንጭ የሆኑ የተከማቹ ብረቶች መያዙ ተገልጿል፡፡

በመድረኩ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽን፣ ጀነራሎች፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል፡፡

በትዝታ ደሳለኝ እና ዙፋን ካሳሁን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.