Fana: At a Speed of Life!

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአንድ ቀን 100ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአንድ ቀን 100ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተሰብስቧል፡፡

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፥ አዲስ ታሪክ ተጻፈ ሲሉ ለግድቡ በ24 ሰዓት 100ሺህ የአሜሪካ ዶላር መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡

ዲያስፖራው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እያደረገ ያለው ድጋፍ ከ60 ሚሊየን በላይ ህዝብ ለመጀመሪያ ጊዜ ብርሃን እንዲያይ ምክንያት እየሆነ ነውም ብለዋል፡፡

ለተደረገው ድጋፍም አምባሳደሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራን አመስግነዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.