Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ዩናይትድ እና ስፖርቲንግ ሊዝበን በብሩኖ ፈርናንዴዝ ዝውውር ተስማምተዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥር ወር የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሊዘጋ ሁለት ቀናት ቀርተውታል።

ክለቦችም ራሳቸውን ለማጠናከር በዝውውር መስኮቱ እየተሳተፉ ይገኛል።

ለረጅም ጊዜያት የፖርቹጋላዊው አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ፈላጊ ሆኖ የቆየው የእንግሊዙ ማንቼስተር ዩናይትድ ፍላጎቱን ለማሳካት ተቃርቧል።

የላንክሻየሩ ክለብ ከፖርቹጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን ጋር በተጫዋቹ የዝውውር ዋጋ ስምምነት ላይ መድረሱ እየተነገረ ነው።

ክለቡ ለተጫዋቹ የተጠየቀውን እስከ 68 ሚሊየን ፓውንድ የሚደርስ የዝውውር ሂሳብ ለመክፈል መስማማቱን የዘገባዎች ያመላክታሉ።

Deal close: Manchester United finally agree fee for Bruno Fernandes with Sporting

ዩናይትድ ለተጫዋቹ በቅድሚያ 46 ነጥብ 6 ሚሊየን ፓውንድ የሚከፍል ሲሆን፥ ቀሪው ሂሳብ ተጫዋቹ በኦልድ ትራፎርድ በሚኖረው ቆይታ እየታየ የሚከፈል ይሆናል።

ፈርናንዴዝም የዝውውር ሂደቱን ለመጨረስ እንግሊዝ ዛሬ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል ማንቼስተር ዩናይትድ አርጀንቲናዊው ተከላካይ ማርኮስ ሮሆ ወደ ሃገሩ ክለብ ኢስቱዲዬንቴስ በውሰት እንዲያመራ ፈቅዶለታል ተብሏል።

ሮሆ በቀድሞው የላዚዮ፣ ፓርማ፣ ማንቼስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ አማካይ በሚሰለጥነው ክለብ እስከ ክረምቱ ድረስ የሚቆይ ይሆናል።

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ደግሞ ስፔናዊውን ተከላካይ ፓብሎ ማሪን በስድስት ወራት የውሰት ውል ለማስፈረም መስማማቱ ታውቋል።

ክለቡ ተጫዋቹን በቋሚነት የማስፈረም አማራጭ ባለው የ4 ሚሊየን ፓውንድ ውሰት ውል ነው ለማስፈረም የተስማማው።

በሌላ በኩል ቶተንሃም ሆትስፐርስ የኔዘርላንድሱን አጥቂ ስቴፈን በርግዊንን ከፒ ኤስ ቪ አይንድሆቨን አስፈርሟል።

ሜትሮ፣ ደይሊ ሜይል እና ኤክስፕረስ የመረጃዎቹ ምንጮች ናቸው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.