Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 6 ወራት ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ባለፉት ስድስት ወራት ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 33 ቢሊየን ዶላር ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በግማሽ ዓመቱ 1 ነጥብ 66 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት አቅዶ ነው ይህን ገቢ ማግኘት የቻለው፤ ይህም የእቅዱን 80 በመቶ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የዘንድሮው የግማሽ ዓመት የወጪ ንግድ አፈፃፀም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ10 በመቶ ብልጫ እንዳለውም ተገልጿል፡፡

የአገዳ ሰብሎች፣ የተፈጥሮ ሙጫ እና እጣን፣ ጫት፣ አበባ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ እንዲሁም ኤሌክትሪክ በበጀት ዓመቱ 6 ወራት ከተያዘላቸው እቅድ በላይ አፈጻጸም ማስመዝገባቸው ተገልጿል፡፡

ባህር ዛፍ፣ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት እንዲሁም ቡና የእቅዱን ከ75 በመቶ እስከ 99 በመቶ አፈጻጸም አስመዝግበዋል፡፡

መጠጥ እና ፋርማሲዩቲካል፣ የቁም እንስሳት፣ ወተት እና የወተት ተዋዕጽኦ፣ ማር እና ማዕድናት ዝቅተኛ አፈፃፀም ካስመዘገቡ ምርቶች መካከል መሆናቸው ተጠቅሷል።፡

ከዘርፍ አፈፃፀም የግብርና ምርቶች ቀዳሚውን ቦታ ሲይዙ የማምረቻው ዘርፍ ውጤቶች፣ ማዕድናት እና ሌሎች ምርቶች ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሠራሩን ለማዘመን እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ ገልፀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.