Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ ከፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ ከፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዢያን ባብቲስት ሌሞይን ጋር ተወያዩ።

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የሚመራ ከፍተኛ መኮንኖችን የያዘው የኢትዮጵያ ልዑክ ከትናንት ጀምሮ በፈረንሳይ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።

በዛሬው እለትም የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ ከፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዢያን ባብቲስት ሌሞይን ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በፈረንሳይ መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጎልበት ተስማምተዋል።

በፈረንሳይ ፓሪስ ጉብኝት እያደረገ ያለው በመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የሚመራ ከፍተኛ መኮንኖችን የያዘው ልዑክ በቆይታው ከፈረንሳይ የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ሃላፊዎች፣ የመከላከያ ሚኒስትርና የኤታ ማዦር ሹም ጋር ውይይት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

የልዑካን ቡድኑ የጉብኝት ዓላማ በአየርና በባህር ሃይል ዘርፎች በሚሰጥ ስልጠና እንዲሁም የወታደራዊ ቁሳቁስ አቅርቦትን አስመልክቶ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ያተኩራል ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.