Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ምዕራብ ሪጅን ከተሞች የኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮ-ቴሌኮም በማዕከላዊ ምዕራብ ሪጅን ከተሞች የኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት አስጀመረ።
ኩባንያው በዛሬው እለት ያስጀመረው የአራተኛው ትውልድ (4ጂ) ኤል.ቲ.ኢ ከፍተኛ አጠቃቀም በሚታይባቸው 103 ከተሞች አገልግሎት ለማስፋፋት የያዘውን እቅድ አንዱ አካል ነው ተብሏል።
በዛሬው ዕለት በማዕከላዊ ምዕራብ ሪጅን በሚኙ አምስት ከተሞች የአድቫንስድ 4 ጂ ኤል.ቲ.ኢ. የሞባይል ኢንተርኔት ማስፋፊያ ፕሮጀክት አጠናቅቆ አገልግሎት ማስጀመሩን ገልጿል።
በዚህም አገልግሎቱ የአምቦ ከተማን ጨምሮ ቡራዩ፣ ሆለታ፣ ወሊሶ እና ሰበታ ከተሞችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ነው የተገለፀው፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፥ በአምቦ በተካሄደው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ በማዕከላዊ ምዕራብ ሪጅን 334 ሺህ ደንበኞች መኖራቸውን ገልጸዋል።
በአምስቱ ከተሞች 125 ሺህ የዳታ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው ፥ በአምቦና አካባቢው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት መጀመሩም የነዋሪዎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያሳድገዋል ብለዋል።
ኩባንያው በቀጣይም የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት የማስፋፊያ ስራዎችን በማጠናቀቅ በተለያዩ የክልል ከተሞች አገልግሎቱን በቅርቡ ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.