Fana: At a Speed of Life!

ለህልውና ዘመቻው የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት- የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝቡ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንን ለመቅበር ለህልውና ዘመቻው የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡
የወጣቶች አንድ መሆን እና መደራጀት ለአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ከእግር እሳት በላይ ስለሚያቃጥለው÷ ወጣቱ መደራጀት፣ መሠልጠን፣ መዝመት እና ሀገሩን ከእናት ጡት ነካሾች አፍራሽ ተልዕኮ መጠበቅ የባህርዳር ወጣቶች ለአሚኮ ገልጸዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነት ምን እንደሆነ በመረዳት ለሕልውና ዘመቻው ያለውን አማራጭ ሁሉ አሟጦ መጠቀም እንደሚገባውም ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው የትህነግ ቡድን ዛሬም ኢትዮጵያዊነትን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ለመነጠል የሚያደርገውን ጥረት ለማክሸፍ ሕዝቡ ቡድኑን ለመቅበር ያለውን አሟጦ ለህልውና ዘመቻው ማዋል እንደሚገባውም አስገንዝበዋል፡፡
“ያለችን አንድ ሀገር ብቻ ናት” ያሉት ነዋሪዎቹ የሀገሪቷን ሉዓላዊነትን አስጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ የጋራ ሥራ መሥራት ይጠበቃል ብለዋል፡፡
አያይዘውም አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ለመደምሰስ የስንቅ ዝግጅቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።
“ሁሉም በየአካባቢው በመደራጀት እንደ አቅሙ የሕልውና ዘመቻውን መደገፍ አለበት÷ እኛም የበኩላችንን እየተወጣን ነው” ብለዋል፡፡
ወጣቶች ሠርጎ ገቦችን በመቆጣጠር ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ጊዜ የማይሠጠው ተግበር መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባልም ነው ያሉት።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.