Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ለ3ተኛ ጊዜ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ከ2ሺህ በላይ ሰንጋዎችን ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
የክልሉ ህዝብ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እያደረገ ያለው ድጋፍ ለጠላቶቻችን አንድ መሆናችንን ያሳየ ተግባራዊ መልስ መሆኑን በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ገልፀዋል፡፡
ከክልሉ ብሄር ብሄረሰቦች የተውጣጡ 2ሺህ 87 ሰንጋዎችንና 500 በግና ፍየሎችን አቶ ተስፋዬ በቢሾፍቱ ከተማ ለሀገር መከላከያ ሰራዊትአስረክበዋል፡፡
ህብረተሰቡ በአይነት እና በገንዘብ ከሚያደር ገው ድጋፍ በተጨማሪ ልጆቹን ወደ ግንባር መርቆ በመሸኘት የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም አቶ ተስፋዬ ጠቁመዋል።
ይበታተናሉ ሲሉን ለነበሩ ሁሉ አንድ መሆናችንን በተግባር ማስመስከር ችለናል ሲሉም ጠቁመዋል።
በክልሉ 500 ሚሊየን ብር ለማዋጣት መታቀዱን የተናገሩት አቶ ተስፋዬ÷ከዚህ ቀደም 113 ሚሊየን ብር ድጋፍ መደረጉን አብራርተዋል።
የክልሉ ህዝቦች ለመከላከያ ሰራዊቱ ማጠናከሪያ እያደረጉት ያለው ድጋፍ አጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
የክልሎች ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስተባባሪ ዶክተር ተመስገን ቡርቃ በበኩላቸው የሀገራችን መደፈር ያሳዘነው መላው ህዝባችን ቀፎው እንደተነካ ንብ ሆ ብሎ በመነሳት ለመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፉን እየገለጸ ነው።
3 ቢሊየን ብር ድጋፍ ለማሰባሰብ መታቀዱንም አስረድተዋል።
የደቡብ ክልል ህዝብ እና መንግስት በዛሬው እለት ለመከላከያ ያደረገው ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን ወደ 128 ሚሊየን ብር ነው ብለዋል፡፡
ብርጋዴል ጀነራል አስረስ አያሌው በበኩላቸው የደቡብ ክልል የህግ ማስከበር እና የህልውና ዘመቻ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እያደረገ ያለው ድጋፍ ከፍተኛ ነው።
በዚህም ህዝቡ ደም ከመለገስ ጀምሮ በሞራል እና በድጋፍ ሰልፍ ያደረገው አስተዋጽኦ በቀላሉ የሚገመት ብለዋል፡፡
አሸባሪውን በአጭር ጊዜ በመደምሰስ ህዝባችን ወደ ልማት ስራ እንዲመለስ ማድረግ አለብንም ነው ያሉት፡፡
ኢትዮጵያን ለማዳን የምናደርገውን እንቅስቃሴ ማጠናከር አለብን ያሉት ጀነራሉ÷ ከክልሉ ህዝብና መንግስት ለተደረገው ድጋፍ በመከላከያ ሚኒስቴር ስም ምስጋና ማቅረባቸውን ከደቡብ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.