Fana: At a Speed of Life!

በጋይንት ግንባር ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት፣ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ ጎጃም ዞን፣ የደብረማርቆስ ከተማና የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደሮች በጋይንት ግንባር ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ የቁም እንስሳትና ደረቅ ሬሽን ድጋፍ አደረጉ።

አስተዳደሮቹ ድጋፉን ዛሬ ለደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ አስረክበዋል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደርና የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር እስካሁን በአራት ዙር በሁሉም ግንባር ለሚገኘው ሰራዊት 26 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን÷ ዛሬ ያስረከቡት ድጋፍ 11 ሚሊየን ብር የሚገመት ነው ተብሏል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዛሬ ያስረከበው ድጋፍ 10 የእርድ ከብትና 22 በግና ፍየል መሆኑ ታውቋል።

አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው እየተደረገ ያለው ድጋፍ መቼም የማይረሳ ነው ብለዋል።

ድጋፉ በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ድጋፉን ያደረጉ አስተዳደሮች ተናግረዋል ።

በዙፋን ካሳሁን እና በምንይችል አዘዘው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.