Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራልና የክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች የጋራ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራልና የክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች የጋራ ጉባዔ እየተካሄደ ነው።

በጉባዔው መክፈቻ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በአሁኑ ሰዓት የህግ ታራሚዎች ሰብአዊ መብት አያያዝ የተሻሻለ ቢሆንም ዘላቂ በሆነ መልኩ መሻሻል ላይ ለመድረስ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

“ማረሚያ ቤቶች የትምህርትና የሥልጠና ቦታ መሆናቸውን በዝዋይ ማረሚያ ቤት በተካሄደው ጉብኝት አረጋግጠናል” ያሉት ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ፥ እንደዚህ አይነት ተግባራትን አጠናክሮ በመቀጠል የትምህርትና የምርት ማዕከላት እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባ አንስተዋል።

ጉባዔውን በመጠቀምም የአፈፃፀም መሻሻሎችን የጋራ ማድረግና ተቋሙን ከቴክሎጅ ጋር በማዋሃድ የማረሚያ ቤቶችን ትስስር ማጠናከር እንደሚስፈልግም ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ ተናግረዋል፡፡

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዳመነ ዳሮታ በበኩላቸው ÷ማረሚያ ቤቶች ቀደም ሲል እንደነበረው ዜጎች የሚታፈኑበት፣ ግፍና ሰቆቃ የሚደርስባቸው ቦታዎች ሳይሆኑ ህገ-መንግስታዊ ስርዓታችን ባስቀመጠው መሠረት ታርመውና ታንፀው፣ አምራችና ህግ አክባሪ ሆነው ወደ ሠላማዊ ህይወት የሚመለሱባቸው ተቋማት መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በጉባኤው ላይ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት እየተሳተፉ ሲሆን ጉባኤው ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ከፌደራል ማረሚያ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.