Fana: At a Speed of Life!

ለህዝብ ሲሉ ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡት የንግድ ባንክ ጥበቃ አቶ ዘውዱ ንጋቴ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ ዘውዱ ንጋቴ እኔ ሳልሞት ጁንታው የህዝብ ንብረት አይዘርፍም በማለት እስከ መጨረሻው ተዋግተው ህይወታቸው ያለፈ የንግድ ባንክ ጥበቃ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነፋስ መውጫ ቅርንጫፍ የረጅም ጊዜ የጥበቃ ሰራተኛ የነበሩት አቶ ዘውዱ የሽብር ቡድኑ ወደ ነፋስ መውጫ ከተማ እንደገባ በቀጥታ ወደ ባንኩ ነበር ያመራው።

ጁንታው ወደ ባንኩ ከመግባቱ በፊት ግን ከአቶ ዘውዱ ብርቱ ትግል ገጥሞት የነበራቸውን አንድ ካዝና ጥይት እስከሚጨርሱ ተዋግተው በርካታ የጁንታውን አባላት ከገደሉ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው አልፏል።

የ56 ዓመቱ አቶ ዘውዱ የስድስት ልጆች አባት ሲሆኑ ልጆቻቸው በአሁኑ ሰዓት ደጋፊ እንደሌላቸው ባለቤታቸው ወይዘሮ ሽንብራ አለነ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት ተናግረዋል።

እንደ ባለቤታቸው ገለፃ ነሐሴ 6 ቀን 2013 ዓ.ም በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው ካለፈ በኋላ ለሶስት ቀን አስከሬን አታነሱም አትቀብሩም እንዲሁም አታለቅሱም በማለት ኢ -ሰብዓዊ ድርጊት ተፈጽሟል።

በባለቤታቸው ገቢ ሲተዳደሩ የነበሩት ወይዘሮ ሽንብራ በጁንታው ቡድን ያላቸው ንብረት ተዘርፏል አሁን ላይ ልጆቻቸውን ለማስተዳደር አቅም እንደሌላቸውም ይናገራሉ።

የሽብር ቡድኑ በደቡብ ጎንደር በቆየባቸው 10 የወረራ ቀናት በርካታ ንፁሃንን ገድሏል፣ ሴቶች እናቶችን ደፍሯል፣ በርካታ ንብረቶችን ዘርፏል እንዲሁም መውሰድ ያልቻለውን አውድሟል፡፡

በዙፋን ካሳሁን እና በምንይችል አዘዘው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.